Sheger FM

Sheger FM

Pop, Talk, Hits, News

Radios Similaires

Comments (0)

Trier par:

No comments yet. Be the first to share your thoughts!
À propos de la radio

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ መስከረም 23 ቀን 2000 ዓ.ም ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡ ይህ ከአዲስ አበባ በ250 ኪሎ ሜትር ክበብ ውስጥ ፕሮግራም እንዲያሰራጭ ፈቃድ አግኝቶ የረጅም ጊዜ የሬዲዮ ሥራ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተቋቋመው ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአድማጮች ዘንድ ተወዳጅነትን ሊያተርፍ ችሏል፡፡ ሸገር 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡ የሸገር ዓላማ ከወገናዊነት የነፃ ትክክለኛ የሕዝብ ድምፅ መሆን፣ ሥነ ምግባርን የጠበቀ የጋዜጠኝነት መርህን መከተልና የተሣካለት የኢንፎቴይመንት (information & entertainment) ሬዲዮ ጣቢያ መሆን ነው፡፡ ጣቢያችን ለማንም ባለመወገን ለሁሉም በታማኝነትና በመልካም ሥነ ምግባር መልካም አገልግሎት በመስጠት የሚያምንና ለእነዚህም እሴቶች ትልቅ ክብር የሚሰጥ ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡

Radios Similaires